GGAA 5th Years Annversary

GGAA 5ኛ ዓመት አብረን የጻፍነው የስኬት ታሪክ!

አምስት ዓመታት በቁጥር ብቻ ሲታዩ ጊዜ ናቸው፤ ለእኛ ግን የትጋት፣ የመተማመን፣ የትብብር እና የስኬት ጉዞ ናቸው።

በGGAA – Gedewon Gebre Authorized Accountancy Firm 5ኛ ዓመት ክብረ በዓላችንን በሀዋሳ ቢሮአችን በደማቅ ሁኔታ አክብረናል።

GGAA 5th Years Anniversary

አርብ ነሐሴ 29

የአዲስ አበባና የሀዋሳ ቢሮ ባለሙያዎቻችን በሀዋሳ ቢሮ በጥቂት ደንበኞቻችን ጋር ተሰባስበን የ5ኛ ዓመታችንን በዓል አክብረናል።

GGAA-5th-Years-Anniversary

ቅዳሜ ነሐሴ 30

የGGAA የአዲስ አበባና የሀዋሳ ቢሮ ባለሙያዎች ብቻ በመሆን በወንዶ ገነት በደማቅ ሁኔታ ተሰባስበን የ5ኛ ዓመት የጋራ ደስታችንን እና ትውስታችንን አጋርተናል።

GGAA 5th Years Anniversary (3)

ለእናንተ ልዩ ምስጋና

GGAA ዛሬ ባለበት ደረጃ እንዲደርስ በተለያዩ ጊዜያት በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በንብረት፣ በምክር፣ በጸሎት እና በሁሉም መንገድ ከጎናችን ለነበራችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።

ለእናንተ ልዩ ምስጋና

  • GGAA ዛሬ ባለበት ደረጃ እንዲደርስ በተለያዩ ጊዜያት በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በንብረት፣ በምክር፣ በጸሎት እና በሁሉም መንገድ ከጎናችን ለነበራችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።
  • በተለይም ውድ ደንበኞቻችን፣ እምነታችሁን ለGGAA ስለሰጣችሁ፣ ከእኛ ጋር ስለቆያችሁ እና ለሌሎችም ስለመከራችሁን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
  • እናንተ የGGAA ደንበኞች ብቻ አይደላችሁም — የጉዟችን አካል ናችሁ!
  • ዛሬ 5ኛ ዓመት፤ ነገ ትልቅ ራዕይ!
  • ይህ 5ኛ ዓመት የጉዟችን መጨረሻ ሳይሆን የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው።
  • በቀጣይም የሙያችንን የላቀ ደረጃ፣ የሙያ ሥነ-ምግባር፣ ታማኝነት እና የደንበኞቻችንን እርካታ በመጠበቅ፣ በተፈቀደልን የሙያ ወሰን ውስጥ በቅንነት፣ በትጋት እና በሙያዊ ብቃት እንደምናገለግላችሁ ቃል እንገባለን።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *